የአቮካዶ ሰላጣ

  • 1
  • 15 ደቂቃ
  • 8 ግብአቶች

የአሰራር ሂደት 1:  አቮካዶ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ አረንጓዴ የፈረንጅ ቃሪያ፣ ኪያር፣ ቲማቲም፣ የድንብላል ቅጠል እና የሎሚ ጭማቂ በአንድ ትልቅ ሳህን ውስጥ በመክተት በደንብ ያዋህዱ፡፡ በመጨረሻም ጨው በመጨመር ማዋሃድና መመገብ ይቻላል፡፡

ግብአቶች:  2 ተልጦ የተከተፈ አቮካዶ፣ 1 ራስ የተከተፈ ሽንኩርት፣ 1 የተከተፈ አረንጓዴ የፈረንጅ ቃሪያ፣ 1 የተከተፈ ኪያር፣ 1 ቲማቲም የተከተፈ፣ ¼ ስኒ በደቃቁ የተተፈ የድንብላል ቅጠል፣ ግማሽ የሎሚ ጭማቂ እና ጨው።

ስኳር ድንች-ሙዝ ለስላሳ

  • 1
  • 15 ደቂቃ
  • 4 ግብአቶች

የአሰራር ሂደት 1:  - በቅድሚያ በሞቀ ኦቨን ምድጃ ውስጥ ስኳር ድንች ይጨምሩና እና ለ 1 ሰዓት ያህል ያበስሉ፤ ቆዳውን በመላጥ በማቀዝቀዣ ውስጥ ያሳድሩት፣

የአሰራር ሂደት 2:  - ስኳር ድንቹን፣ ሙዝ፣ አኩሪ አተር ወተት እና ቀረፋውን በአንድ ላይ በማዋሃድ ለስላሳ እስኪሆን ድረስ መፍጨትና ማዘጋጀት፡፡

ግብአቶች:  1 ትልቅ ስኳር ድንች፣ 1 ሙዝ፣ 2 ኩባያ የአኩሪ አተር ወተት እና ¼ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ቀረፋ።

የተልባና እንጆሪ ለስላሳ

  • 1
  • 5 ደቂቃ
  • 4 ግብአቶች

የአሰራር ሂደት 1: - 1- የአኩሪ አተር ወተት፣ እንጆሪ፣ ሙዝ እና የተልባ እህል ወደ ጁስ መፍጫ ውስጥ በመጨመር ለስላሳ እስኪሆን ድረስ መፍጨት፤ ከዛም ወደ ብርጭቆ በመቅዳት ማጣጣም ።

ግብአቶች:  1 ኩባያ የአኩሪ አተር ወተት፣ ኩባያ የቀዘቀዘ እንጆሪ፣ ½ የቀዘቀዘ ሙዝ እና 2 የሾርባ ማንኪያ የተልባ እህል


የድንች ሰላጣ

  • 1
  • 15 ደቂቃ
  • 7 ግብአቶች

የአሰራር ሂደት 1:  - የጨው ውሃ በያዘ ድስት ውስጥ ድንቹን ይጨምሩ እና በድንብ እስኪበስል ድረስ ያቆዩት፡፡ ከቀዘቀዘ በኋላ ልጦና ከትፈው የዘጋጁ፤ በተመሳሳይ እንቁላሉን በሌላ ድስት ከ 10 እስከ 12 ደቂቃ ያህል ይቀቅሉ፤ ሲቀዘቅዝ ሽፋኑን በመላጥ ከትፈው የዘጋጁ፣

የአሰራር ሂደት 2: - ድንቹን, እንቁላል, ሴሊየሪ, ሽንኩርት, ማዮኔዝ, ሰናፍጭ, ነጭ ሽንኩርት ዱቄት እና ጨው በአንድ ትልቅ ሳህን ውስጥ በመክተት ያዋህዱ፣ በደንብ ሲቀላቀል ትንሽ አቀዝቅዞ መመገብ።

ግብአቶች:  ተልጦ የተዘጋጀ ድንች፣ 3 እንቁላል፣ 1 ስኒ የተከተፈ ሴለሪ፣ ግማሽ ስኒ የተከተፈ ሽንኩርት፣ ¼ ስኒ ማዮኔዝ፣ 1 የሾርባ ማንኪያ መስታርድ እና ¼ የሾርባ ማንኪያ ነጭ ሽንኩርት።

የእርጎ ፓንኬክ

  • 1
  • 20 ደቂቃ
  • 4 ግብአቶች

የአሰራር ሂደት 1:  - እርጎውን በሳህን ውስጥ ጨምረው እንኪለሰልስ ድረስ በማንኪየ መምታት፣ ከዛም እንቁላሉን በመጨመር መምታት

የአሰራር ሂደት 2:  - ዱቄቱንና ቤኪንግ ሶዳውን ከእርጎው ውህድ ውስጥ በመጨመር በደንብ መቀላቀል

የአሰራር ሂደት 3:  - በመካከኛ ሙቀት ላይ ትንሽ ዘይት ያለው መጥበሻ ላይ ሊጡን በትልቅ ማንኪያ በመጨለፍ ያድርጉት፡፡ ከዛም ከ3 እስከ 4 ደቂቃዎች ድረስ ያብሱ። ቀጥሎም በሌላኛው በኩል በመገልበጥ ቡናማ እስኪሆን ድረስ ከ 2 እስከ 3 ደቂቃዎች ያዙሩት እና ያብሱ።

ግብአቶች:  168 ግራም እርጎ፣ 1 እንቁላል፣ ግማሽ ስኒ የፍርኖ ዱቄት እና 1 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ

ፍላፊ ፍሬንች ቶስት

  • 1
  • 20 ደቂቃ
  • 8 ግብአቶች

የአሰራር ሂደት 1: - በትልቅ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ዱቄቱን ለክተው በመጨመር ከወተቱ ጋር የዋህዱ፣ ከዛም ለስላሳ እስኪሆን ድረስ እንቁላል, ስኳር, ቫኒላ, ቀረፋ እና ጨው በመጨመር ዋህዱ

የአሰራር ሂደት 2: - አነስ ባለ እሳት ላይ መጥበሻ ይጣዱ

የአሰራር ሂደት 3: - የዳቦ ቁርጥራጮቹን/ስላይስ በወተት ውህድ ውስጥ እስኪርስ ድረስ መንከር

የአሰራር ሂደት 4: - ከዛም እያንዳንዱን ዳቦ ባሞቅነው መጥበሻ ላይ ወርቃማ ቡናማ እስኪሆን ድረስ ማብሰል ፤ በመጨረሻም በትኩሱ ማቅረብ።

ግብአቶች:  ¼ ኩባያ የፍርኖ ዱቄት፣ 1 ኩባያ ወተት፣ 3 እንቁላል፣ 1 የሾርባ ማንኪያ ነጭ ስኳር፣ 1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ፣ ½ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ቀረፋ እና በስሱ የተሸነሸን ዳቦ ።